ያየ አለ (Yaye Ale)

ያየ አለ…
ያየ አለ…
ያየ አለ ሆዴ ምን ጎርሶ እንደዋለ
ያየ አለ…
ያየ አለ…
ያየ አለ ሆዴ ምን ጎርሶ እንደዋለ

ምን አግኝቶ አማረበት አሉኝ
ችግር አያውቅ ብለው ተረቱብኝ
አልተራብኩም ጥርሴንም አልከፋው
መሳቁ እንጂ ማኘኩ መች ጠፋው
ለምን ልዘን ቀለለልኝ እዳ
ሲያስቡለት የራቀ ላይጎዳ

ዛሬ አበቃ ተረዳሁኝ
መላም አገኘሁኝ
ተወት አርጎ የታገሰ
ማን ከማን አነሰ

አዙሮ ካላየ ሆድዬ አንገት እንደሌለው
መች ይበጃል ወዳጅ አንችዬ ሆድ እማይናፍቀው
አዙሮ ካላየ ሆድዬ አንገት እንደሌለው
መች ይበጃል ወዳጅ አንችዬ ሆድ እማይናፍቀው

በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
እንዴት አረገሽ
በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
ከምኑ ጣለሽ

ያየ አለ …
ያየ አለ …
ያየ አለ ሆዴ ምን ጎርሶ እንደዋለ
ያየ አለ …
ያየ አለ …
ያየ አለ ሆዴ ምን ጎርሶ እንደዋለ

ዋልኩኝ ቤቴ ጓዳዬን ሳሞቀው
ዞራ ገባች ትርፏንም ሳታውቀው
ተረድቼው የማሽላን ዘዴ
ጥርሴ ሳቀ ምን ቢቃጠል ሆዴ
ጤና ካለኝ ምኑ ሊጎልብኝ
ገላ አልዋስ ችግርም የለብኝ

ካልሆንሽለት እንደ አሳቤ
ይርቅሻል ልቤ
በወደደ ወዳጅ ባለ
የሞተ ማን አለ

ምን ያባክነኛል ሆድዬ ልሳቅ እያየሁሽ
እንደ ሐምሌው ዝናብ አንችዬ ዞረሽ ካገኘሁሽ
ምን ያባክነኛል ሆድዬ ልሳቅ እያየሁሽ
እንደ ሐምሌው ዝናብ አንችዬ ዞረሽ ካገኘሁሽ

በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
እንዴት አረገሽ
በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
ከምኑ ጣለሽ
በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
እንዴት አረገሽ
በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
ከምኑ ጣለሽ
በይ መሄድሽ በይ መዞርሽ
እንዴት አረገሽ

Scroll to Top